Switch to App

ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆነው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ወደ መከላከያ ሲቀላቀል የሌሎች ክልሎች ልዩ ኃይሎች 75% በሲቪል ስራ ላይ እንዲሰማሩ ይደረጋል።

ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆነው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ወደ መከላከያ ሲቀላቀል የሌሎች ክልሎች ልዩ ኃይሎች 75% በሲቪል ስራ ላይ እንዲሰማሩ ይደረጋል። ወልቃይትን እና ራያን በአዲሱ የትግራይ አስተዳደር ሥር አድርጎ ሪፍረንደም ለማካሄድ መታሰቡ”፣ የአማራን ልዩ ሃይል ሙሉ በሙሉ ትጥቅ ለማስፈታት መንግሥት ማቀዱ እያነጋገረ ነው ።

መንግስት አዲስ ትዕዛዝ ሰቷል ፤የክልል ልዩ ሀይል የተባለው ወታደራዊ አደረጃጀት መሉ በሙሉ እንዲፈርስ ትዕዛዝ ተላልፏል። ልዩ ሀይሉ ሲፈርስ በተለየ ሁኔታ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ወደ መደበኛ መከላከያ ስራዊት የሚቀላቀሉ ሲሆን 30ኛው እና 31ኛው ዙር ሰልጣኞች መደበኛ ፖሊስ ሆነው ይቀጥላሉ ተብሏል። ይህ የተሰጠው ትዕዛዝ ለኦሮሚያ ሲሆን ሌሎች ክልሎች ላይ ያሉ ልዩ ኃይሎች ፈርሰው 25% ወደ ክልል ፖሊስነት ሲቀየሩ 75% አስፈላጊውን የአገልግሎት ዘመን ክፍያ ተሰቷቸው በሲቪል ስራ ላይ እንዲሰማሩ ይደረጋል።

ከ 31 ዙር በላይ በመሰልጠን ያስመረቀውን የኦሮሚያ ልዮ ሃይል ሳያፈርስ ሌላው ክልል ልዮ ሀይሉን እንዲያፈስ መጠየቅ አይቻልም:: እንደሚታወቀው የኦሮሚያ ልዮ ሀይል የሚሉት በቁጥር ከአንድ ሚልዮን ይበልጣል:: በውስጡም ብዙ የኦነግ ወታደር የነበሩትን ቀጥሮ ደምወዝ የሚከፍል ሃይል ነው::

ይህ ሃይል ከአውሮፕላንና ታንክ በስተቀር እጅግ በጣም ዘመናዊ የሚባሉ መሳሪያዎች ከኢራን ህንድና ሰሜን ኮሪያ በህገወጥነት በኢትዮጵያውያን ታክስ ተገዝቶ እንዲታጠቅ ተደርጓል:: የኦሮሚያ ልዮ ሀይል ባለፉት አምስት አመታት የአማራ ህዝብ በተለያዮ ዞኖች ጥቃት ሲፈፀምበት አብሮ ሲያጠቃ የቆየ ሃይል ነው::

አብይ አህመድ ያሰበው ባለፈው በኢትዮ 360 ሰበር ዜና ላይ እንደተገለፀው ይህን ሀይል ወደ መከላከያው በማስገባት የመከላከያ ተቋምን ሙሉ ለሙሉ በመቆጣጠር ሊያደርግ ያሰበውን ወረራና ጭፍጨፋን ህጋዊ ሽፋን ለመስጠት ነው:: ስለሆነም የሲዳማ የአማራ የደቡብ የአፋር የሱማሌ የቤንሻንጉል የጉራጌ የወላይታ ና የጋምቤላ ህዝብ ይህን ውጥን በደንብ በማጤን እንዳትቀበለው ትመክራለህ::

የየክልሉ ልዩ ሃይል እንዲፈርሱ በመርህ ደረጃ የተወሰነው ትክክል ነው።ሆኖም ሀወሃት ከባድና የቡድን መሳሪዎች በታጠቀበት፣የሰራዊት ስልጠና በሚሰጥበት፣ የአማራና አፋር ክፈተኛ ስጋት ሆኖ ሳለ፡ለምን አሁን ተፈለገ? ለወልቃይትና ራያ ምን ታስቦ ነው?